News
አስደሳች ዜና!
2nd August, 2024
የአጥንት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት እና የመገጣጠሚያ ቅየራ እንዲሁም የአርትሮስኮፒ ህክምና ሠብ ስፔሻሊስት ሃኪም በሆኑት ዶ/ር ሰኢድ መሐመድ የሚመራው የሙሉ ዳሌ እና ጉልበት መገጣጠሚያዎች ቅየራ ከፍተኛ ቀዶ ህክምና በተቋማችን የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በይፋ አገልግሎት መሰጠት ጀመረ ። ይህ አገልግሎት በሃገራችን የፕራይቬት ዊንግ ህክምና ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሠጥ ሲሆን፣ በርካታ የችግሩ ሰለባ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ይጠቀሙበታል ተብሏል ። ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጁ በሚሰጠው ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለመሆን ኘራይቬት ዊንግ ከፍቶ በተመጣጣኝ ዋጋ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ ለማቅረብ በሰፊው እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ስለህክምና አገልግሎቱ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች መደወል፣ አልያም በአካል የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ጎራ ብለው መመዝገብ ይችላሉ::
+251907707082, +251963001972
"የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ"