News
Relationship with hospitals in Japan
4th August, 2024
በዛሬው ዕለት በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ከጃፓን ሃገር ከመጡ የካይዘን ትግበራ ባለሙያዎች ጋር ውይይት ተደረገ። ከጃፓን ሃገር የመጡ የከይዘን ትግበራ ባለሙያዎች ለሁለት አመታት ነፃ አገልግሎት በተቋሙ ለመስጠት ዝግጅታቸውን አጠያቀው በዛሬው ዕለት ስራ ጀምሮዋል ። "JICA Ethiopia" ( Japan International Corporation agency ) የጃፓን መንግስታት ድርጅት የሆነው ይህ ተቋም በሚቆይበት ሁለት ዓመታት በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ጥሩ ቆይታ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል ። ተቋሙ የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በሚያደርጋቸው ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ውስጥ JICA የሚሰጥው የሁለት ዓመት ነፃ አገልግሎት ጥቅሙ ከፍተኛ እንደሆነ ተገልጿል። በመጨረሻም ተቋሙ ለጀመረው 5s activity (five S activity)ን ለማሳደግ ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል ሲሉ የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የአስተዳደርና ልማት ም/ኘሮቮስት የሆኑት አቶ አለሙ ክብረት ገልፀዋል ።
"ሰላም አይለየን"